ስለዚህ ቱልኪት (Toolkit)

ውድ አስተማሪዎች እና የወጣቶች ፕሮግራም አቅራቢዎች፣

በአድቬንቸር በጋ ጊዜ ለማንበብ፣ ለመስራት እና ለማሰስ የመማሪያ ማህበረሰባችሁን አነሳሱ! ይህንን መሳሪያ ለክፍል እና መደበኛ ባልሆኑ አስተማሪዎች በመጨረሻዎቹ ጥቂት ሳምንታት ትምህርት ቤት ወይም በበጋ ካምፖች እና ፕሮግራሞች እንድትጠቀሙበት አዘጋጅተናል። የአድቬንቸር በጋ አስተማሪ ቱልኪታችን ልጆች እንዲያነቡ፣ እንዲሰሩ እና ሁሉንም የበጋ ወቅት እንዲያስሱ ለማድረግ ሁሉንም በአንድ ላይ የሚያገኙበት ግብዓት ነው። የአድቬንቸር በጋ ጋዜጣ፣ ለተንከባካቢዎች እና ለቤተሰቦች የሚሆኑ ጠቃሚ ምክሮች፣ ለሁሉም ዕድሜዎች የሚሆኑ የእንቅስቃሴ ሀሳቦችን እና ሌሎች ከማህበረሰባችሁ ጋር ልታጋሯቸው የምትችሏቸውን ምንጮች ታገኛላችሁ። ትርጉሞች በስፓኒሽ፣ በቬትናምኛ፣ በአረብኛ፣ በሶማሊኛ እና በአማርኛ ይገኛሉ።

የአስተማሪ አገልግሎቶች፦ ለበጋ እና ከዚያም በኋላ 

denverlibrary.org/educators

የአድቬንቸር በጋ መረጃ ክፍለ-ጊዜዎች
በዚህ በጋ ተማሪዎችቻችሁ ለማንበብ፣ ለመስራት እና ለማሰስ እንዲነሳሱ ለማድረግ የቤተ መፃህፍት ሰራተኞች ጋር የጉብኝት ቀጠሮ አስይዙ። ሰራተኞቻችን ስለ የአድቬንቸር በጋ ፕሮግራሞች እና ሽልማቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ያካፍላሉ፣ ለወጣቶች የቅርብ ጊዜ መፅሐፎችን ይመክራሉ፣ በጫወታ የተሞሉ መማሪያ እንቅስቃሴዎችን ይመራሉ እንዲሁም የተሳትፎ ሂደቱን ያብራራሉ። ጉብኝቶች ከእናንተ ፍላጎቶች ጋር ሊጣጣሙ ይችላሉ።

የመፅሐፍ ክለቦች፣ ፕሮግራሚንግ እና ሌሎችም።
ተማሪዎችዎቻችሁን በመፅሐፍ ክለቦች፣ በወጣቶች የሚመሩ የምክር ቦርዶች፣ እንቅስቃሴዎች፣ ዝግጅቶች፣ መሥሪያ ቦታዎች እና ምክሮች ጋር ሁሉንም የበጋ ወቅት እንዲያነቡ፣ እንዲጫወቱ እና እንዲያስሱ እናበረታታለን። denverlibrary.org/SoA ወይም denverlibrary.org/kids. በመጎብኘት በበጋው ወቅት ለመገናኘት እና ለመማር ስላሉት ብዙ እድሎች የበለጠ እወቁ። 

የዓመቱን ሙሉ አገልግሎቶች
ከአስተማሪ ስብስቦች እና ከአስተማሪ ቤተ-መጽሐፍት ካርዶች እስከ ቨርቹዋል የመማሪያ ክፍል ጉብኝቶች እና የአንድ ለአንድ የጥናት እገዛ፣ ዓመቱን ሙሉ ሽፋን እንድታገኙ አድርገናል! ስለ ሁሉም አገልግሎቶቻችን የበለጠ ለማወቅ በአካባቢያችሁ የሚገኘውን ቅርንጫፍ አግኙ ወይም ክፍላችሁን ወይም ቡድናችሁን ከቤተ-መጽሐፍት ጋር ለማገናኘት በማንኛውም ጊዜ ከእኛ ጋር ተወያዩ።